Skip to main content

message of the head

 

የሳይነስና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የተቐዋቐመበትን ግብ ለማሳካት ሥራዎቹ በሙሉ በእቅድ ተደራጅተው መመራት እነዳለባቸው ይታመናል በዋናነት በዞኑ ውስጥ የሚከናወኑ የሳይነስና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ፕሮግራሞች በመንግስት ፖሊሲና አስትራቴጂ ላይ ተመስርተው በተቀናጀና ሁሉ አቀፍ በሆነ እቅድ የሚመሩበትን አሰራር ስርአት በመዘርጋት ወረዳዎችንና ከተማ አስተዳደሮችን በመደገፍና በማቀናጀት በተዘረጋላቸው መርሃ ግብር መሰረት እንዲመሩ መከታተል አፈጻጸማቸውን መገምገምና ለተሻለ ውጤት የሚያበቁ ትምህርታዊ ግኝቶችን በማካተት ቴክኒካል ድጋፍ ይሰጣል የሳይነስና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ስራዎች ከመንግስት የ 10 አመት መሪ እቅድ ጋር ተጣጥመው እነዲሄዱና አፍጻጸሙን እንዲያሳልጡ በዞኑ በሁሉም ሴክተሮች የሳይነስና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ጉልህ ድርሻ አለው ፡፡ ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ የአሰራር ስርአት በመዘርጋት ብቁና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተቀዋማትን ከመፍጠር አንጻር ፤ ውጤታማ የትብብር ስረአትን ከማረጋገጥ አንጻር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች አጠቃቀምና አቅርቦት በማሳደግ የግሉን ዘርፍ የቴክኖሎጂ ውጤታማነትን በማሳደግ ምቸሁ የምርምርና የፈጠራ ስራ ምህዳር በመፍጠር የተመራማሪዎችንና የፈጠራ ባለሙያዎችን ውጤታማነት በማሳደግ ከጨረር አመንጪ መሳሪያዎች በመከላከል የህብረተሰቡን ደህንነት በማረጋገጥ የባለብዙ ዘርፍ አካታች /ስርአተ ጾታ ጸረ-ኤች አይ ቪ እና ስነምግባር ጉዳዮችን በማጎልበት/ የሪፎርም ስራዎችን በማጠናከር የዲጂታል ኢኮኖሚ ስርአትን መገንባት ነው::

የሳይንስና ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት፣

የሳይንስና ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት፣

  • የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና ዉጤታማነትን የሚያሰፍኑ አሰራሮችን መዘርጋት፤
  • በሳይንስና ቴክኖሎጂ የምርምርና የፈጠራ ስራ የሚያከናውኑ አካላትን በመመልመል የቁሳቁስ፣ የቴክኒክና፣ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ስራቸው ለተጨባጭ አገልግሎት እንዲበቃ ማድረግ፤
  • የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበባት በመደበኛ ት/ቤቶች እንዲደራጁና ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን በክልሉ ማህበረሰብ ባህል እንዲሆን በቀጣይነት መስራት፤
  • በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዙሪያ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰብና ተቋማትን በመመልመል ማበረታታትና መሸለም፤
  • በከተሞች የሳይንስ ካፌዎችንና የቴክኖሎጂ ፓርኮች እንዲቋቋሙ ማድረግ፣
  • በመደበኛ ትምህርት ቤቶች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሳምንታት እንዲከበሩ በማድረግ ሁልአቀፍ መነቃቃት እንዲኖር በማድረግ፣