Skip to main content

message of the head

 

የሳይነስና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የተቐዋቐመበትን ግብ ለማሳካት ሥራዎቹ በሙሉ በእቅድ ተደራጅተው መመራት እነዳለባቸው ይታመናል በዋናነት በዞኑ ውስጥ የሚከናወኑ የሳይነስና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ፕሮግራሞች በመንግስት ፖሊሲና አስትራቴጂ ላይ ተመስርተው በተቀናጀና ሁሉ አቀፍ በሆነ እቅድ የሚመሩበትን አሰራር ስርአት በመዘርጋት ወረዳዎችንና ከተማ አስተዳደሮችን በመደገፍና በማቀናጀት በተዘረጋላቸው መርሃ ግብር መሰረት እንዲመሩ መከታተል አፈጻጸማቸውን መገምገምና ለተሻለ ውጤት የሚያበቁ ትምህርታዊ ግኝቶችን በማካተት ቴክኒካል ድጋፍ ይሰጣል የሳይነስና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ስራዎች ከመንግስት የ 10 አመት መሪ እቅድ ጋር ተጣጥመው እነዲሄዱና አፍጻጸሙን እንዲያሳልጡ በዞኑ በሁሉም ሴክተሮች የሳይነስና ኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት ጉልህ ድርሻ አለው ፡፡ ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ የአሰራር ስርአት በመዘርጋት ብቁና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተቀዋማትን ከመፍጠር አንጻር ፤ ውጤታማ የትብብር ስረአትን ከማረጋገጥ አንጻር የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች አጠቃቀምና አቅርቦት በማሳደግ የግሉን ዘርፍ የቴክኖሎጂ ውጤታማነትን በማሳደግ ምቸሁ የምርምርና የፈጠራ ስራ ምህዳር በመፍጠር የተመራማሪዎችንና የፈጠራ ባለሙያዎችን ውጤታማነት በማሳደግ ከጨረር አመንጪ መሳሪያዎች በመከላከል የህብረተሰቡን ደህንነት በማረጋገጥ የባለብዙ ዘርፍ አካታች /ስርአተ ጾታ ጸረ-ኤች አይ ቪ እና ስነምግባር ጉዳዮችን በማጎልበት/ የሪፎርም ስራዎችን በማጠናከር የዲጂታል ኢኮኖሚ ስርአትን መገንባት ነው::

የሴክተሩ አጠቃላ ይሁኔታ

የስልጤ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክሎጂ መምሪያ በዞን ካሉ 27 ሴክተር መስሪያ ቤቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በአሁን ወክት በስልጤ ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ህንፃ ውስጥ ሁለተኛ ፎቅ መቀመጫውን በማድረግ ስራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡ መምሪያው በሶስት ዋናዋና ዳይሬክቶሬቶች እና በሁለት ደጋፊ የስራ ሂደቶች ተዋቅሮ ይገኛል፡፡ ሶስቱ ዋናዋና ዳይሬክቶሬቶች ኢኮቴ መሠረተ ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት፣የሶፍትዌር ድረ-ገጽ ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች ድጋና ክትትል አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ሲሆኑ ሁለቱ ደጋፊ የስራ ሂደቶች ደግሞ የሰው ሀብትና የልማት ዕቅድ ናቸው፡፡ መምሪያው መጀመሪያ ሲቋቋም ሶስት (03) ባለሙያና አንድ (01)ሀላፊ በድምሩ አራት (04) ባለሙያ የነበሩት ሲሆን በአሁን ወክት በዋናዋና የስራ ሂደቶች ሰባት (07) ባለሙያ፣ በደጋፊ የስራ ሂደቶች ደግሞ አምስት (05) ባለሙያ እና አንድ ሀላፊ በድምሩ አስራ አምስት(15) ባለሙያ በመያዝ የተደራጀ ሲሆን በወረዳ እንዲሁም በከተማ አስተዳደር ደረጃ መዋቅር የተዘረጋ በመሆኑ በርካታ ስራዎችን እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍን በማሳደግ ለፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያለውን አስተዋጽኦ በማጎልበት ዞኑን የፈጣን ልማትና ዕድገት ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግና መምሪያው ከዞን እስከ ቀበሌ ባሉ መንግስታዊ ተቋማት ውስጥ የሚሰጠው አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈና የተደራጀ እንዲሆንና አገልግሎት አሰጣጡ ዘመናዊ ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ መልካም አስተዳደርን ማስፈንና የሃብት ብክነትን መቀነስ ነው፡፡